ለአማራ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት

ባህርዳር፣

በድጋሚ የመድሃኒት ግዥ ጨረታ  እንዲወጣልን ስለመጠየቅ

ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚተዳደሩት የመንግስት የልማት ድርጅት አንዱ የሆነው የንጋት ኮርፖሬት አካል  ሲሆን በክልሉ የሚገኘውን የጤና አገልግሎት ጥራት ማሻሻል ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡

ይህንንም መሰረት በማድረግ መድሃኒት ከውጭ ለማስገባት ባወጣው ኢምፖርት ፈቃድ ቁጥር 13132/MEMDICER/2024 መሰረት ከሀገር ውስጥ የመድሃኒት እና የላቦራቶሪ ግብአት አምራች  ድርጅቶች /ፋብሪካዎች/ ጋር ለ2017 ዓ/ም በጀት አመት ለ1 አመት የሚቆይ ውል ይዞ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ድርጅቶች /አምራች ፋብሪካዎች/ የሚያመርቱትን መድሃኒት በአይነት፤ በመጠን እና በግራም በመግለፅ የሚያቀርቡበትን /መሸጫ ዋጋ/ በተጨማሪም ለዚሁ ግብአት የትራንስፖርት አገልግሎት የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ባህርዳር ድረስ  ለማድረስ አገልግሎቱን የሚሰጠበትን ዋጋ አካትተው  በዝርዝር እንዲያቀርቡ  ይጠበቃል፡፡ 

  • ዋጋ ሞልተው ሲያቀርቡ የመድሃኒት አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ EFDA ሰርትፍኬት  እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ አይይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጫራታው በጋዜጣ ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚውልበት ጊዜ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል
  • የጫራታዉ ሰነድ በ 30 /05 /2017 ከጠዋቱ 4፡00 ጫራታው በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ባ/ዳር ተወካዮች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል
  • ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጫራታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡
  • የግብር ከፋይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ቲኦቲ እና የቫት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  • ተወዳዳሪዎች የቴክኒካል ፕሮፖዛል፣የዋጋ ማቅረቢያ እና ሌሎች የጫራታ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ኢንቮሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • ሲኘኦ በባንክ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቃል::

ሰነዱን የሚያቀርቡበት መንገድ በአካል ወይምበፖስታ1555

ስ/ቁ: 0583206668/0583207068

አድራሻ : ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 14 ኖክ አካባቢ ሪየስ ኢንጅነሪንግ ህንፃ 2ኛ ፎቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top