local bid notice
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ----------
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክ 500 ካሬ ሜትር ላይ የሚአርፍ G+2 ህንፃ በማስገንባት በካንሰር ሴንተር እና ዲያግኖስቲክ ሴንተር መክፈት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ እውቀቱና ልምዱ ያላቸውን ሙያተኞች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአዋጭነት ጥናት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
ተግባር1. ባለ 60 አልጋ በካንሰር ሴንተር አዋጭነት ጥናት
ተግባር2. ከፍተኛ ዲያግኖስቲክ ላበራቶሪ አዋጭነት ጥናት
ከተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች የሚጠበቁ ፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር፣የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበትከ 29/12/2016ዓም ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱን ቀበሌ 14 ኖክ አካባቢ ከሚገኘው ሪይስ ኢንጅነሪንግ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ከሚገኘው ከሜዴክስ ዲያግኖስቲክ ቢሮ ውስጥ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው የተቋሙ አድራሻ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው ቀን ከሰዓት በኃላ 7፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. የጨረታ ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ ዋና መ/ቤት በዚሁ እለት ከሰዓት በኃላ 7፡30 ይከፈታል፡፡
5. በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
6. አስረኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የመንግስት የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ጨረታው ይከፈታል፡
7. ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
8.ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0588304550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
10. አሸናፊ ድርጅት ከተለየ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ከተቋሙ ጋር እየተወያዬ መፈፀም ይጠበቅበታል፡፡
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክ